እግዚአብሔር የሰባተኛውን የቅዱስ አቆጣጠር ወር የመጀመሪያ ቀን የመለከት በዓል አድርጎ ሾመው፤ ይህም ጣዖት አምልኮ ውስጥ የወደቁትን እስራኤላውያን ኃጢአት ይቅር ብሎ ሁለተኛውን ዐሥርቱ ትእዛዛት ሲሰጣቸው የነበረውን የስርየት ቀን እንድናስታውስ ነው። ከዚህም በላይ፣ በመለከት በዓል ላይ ንስሐ እንዲገቡ ጥሪ ለማድረግ መለከት እንደሚነፋ ሁሉ፣ ኢየሱስም ወደዚህች ምድር መጥቶ "ንስሐ ግቡ" እያለ የሰው ልጅ ንስሐ እንዲገባ አሳሰበ።
በጠፋው ልጅ ምሳሌና ዮናስ በነነዌ አንድ መቶ ሃያ ሺህ ሰዎችን ወደ ድነት በመምራቱ ታሪክ ውስጥ እንደምናየው፣ ከእግዚአብሔር የሚመጡ ታላላቅ በረከቶች ሁልጊዜ የንስሐ ሥራን ተከትለው ይዘጋጃሉ። ዛሬም እንደ ዮናስ ሁሉ፣ ወደ ዓለም ስለዞሩ አይኖቻችንና ልቦቻችን ፍጹም ንስሐ መግባት አለብን፣ እናም መላው ዓለም ወደ ክርስቶስ አህንሳንግሆንግና ወደ እግዚአብሔር እናት እንዲመለስ ጥሪ እያቀረብን መለከት መንፋት አለብን።
“እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፤ ‘የሰባተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን ዕረፍት ይሁንላችሁ፤ በመለከት ድምፅም የሚከበር የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ።
“የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ስለዚህ እንደየሥራችሁ በእያንዳንዳችሁ ላይ እፈርዳለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። እንግዲህ ንስሓ ግቡ፤ በኀጢአት እንዳትጠፉ፣ ከኀጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።
119 የቡንዳንግ ፖ.ሳ.ቁ፣ ቡንዳንግ-ጉ፣ ሲኦንግናም-ሲ፣ ግዮንጊ-ዶ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ስልክ 031-738-5999 ፋክስ 031-738-5998
ዋና ምስሪያ ቤት፡ 50፣ ሱኒ_ሮ ፣ ቡንዳኔግ_ጉ፣ ሲዮንግያም_ሲ፣ ግዋንጊዶ_ሲ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ዋና ቤተ ክርስቲያን፡ 35፣ ፓንግዮዬክ_ ሮ ቡንዳንግ _ጉ፣ ሶንግያም ሲ፣ ጊዮኔጊ_ዱ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
World Mission Society Church of God ሁሉም መብቶች የተጠብቁ ናቸው። ግላዊ ደኅንነት