በእግዚአብሔር የሚያምኑ ሁሉ የዳስ በዓልን እንደ እግዚአብሔር ትምህርት ማክበር አለባቸው። ይህ የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔር በነቢዩ ዘካርያስ በኩል የዳስ በዓልን ለሚያከብሩ መንፈስ ቅዱስን እንደሚሰጥና ለማያከብሩት ደግሞ ቅጣት እንደሚያመጣ ተናግሮ ስለነበር ነው።
ኢየሱስ በመጀመሪያ መምጣት መንፈስ ቅዱስን ሰጠ፤ በሁለተኛው መምጣት ደግሞ መንፈሱና ሙሽራይቱ በዳስ በዓል መንፈስ ቅዱስን ይሰጣሉ። "መንፈሱና ሙሽራይቱ የሕይወት ውኃን ይሰጣሉ"፣ "ሕያው ውሃ ከኢየሩሳሌም ይፈልቃል፣" እና "የሕይወት ውኃ ወንዝ ከእግዚአብሔር ዙፋን ይፈልቃል" የሚሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ኢየሩሳሌም የሰማያዊት እናት መንፈስ ቅዱስንና ወደ ሕይወት የሚያመሩ ትምህርቶችን እንደምትሰጥ ይተነብያሉ።
የአይሁድ የዳስ በዓል በተቃረበ ጊዜ ግን፣... የበዓሉ መጨረሻ በሆነው በታላቁ ቀን፣ ኢየሱስ ቆሞ ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ አለ፤... በእኔ የሚያምን፣ መጽሐፍ እንዳለ የሕይወት ውሃ ምንጭ ከውስጡ ይፈልቃል።” ይህን ያለው በርሱ የሚያምኑ ስለሚቀበሉት መንፈስ ነበር፤... ዮሐንስ 7፥2–39
መንፈስና ሙሽራዪቱ፣ “ና” ይላሉ፤ የሚሰማም፣ “ና” ይበል፤ የተጠማም ሁሉ ይምጣ፤ የሚፈልግም ሁሉ የሕይወትን ውሃ በነጻ ይውሰድ። ራእይ 22፥17
119 የቡንዳንግ ፖ.ሳ.ቁ፣ ቡንዳንግ-ጉ፣ ሲኦንግናም-ሲ፣ ግዮንጊ-ዶ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ስልክ 031-738-5999 ፋክስ 031-738-5998
ዋና ምስሪያ ቤት፡ 50፣ ሱኒ_ሮ ፣ ቡንዳኔግ_ጉ፣ ሲዮንግያም_ሲ፣ ግዋንጊዶ_ሲ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ዋና ቤተ ክርስቲያን፡ 35፣ ፓንግዮዬክ_ ሮ ቡንዳንግ _ጉ፣ ሶንግያም ሲ፣ ጊዮኔጊ_ዱ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
World Mission Society Church of God ሁሉም መብቶች የተጠብቁ ናቸው። ግላዊ ደኅንነት