እንደተጻፈው፣ “በክርስቶስ ኢየሱስ በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት መኖር የሚወድዱ ሁሉ ይሰደዳሉ፣” እንዲሁም ኢየሱስ እንዳለው፣ “በኋላዬ ሊመጣ የሚፈልግ ማንም ቢኖር . . . መስቀሉንም በየዕለቱ ተሸክሞ ይከተለኝ፣” ለመንግሥተ ሰማያት ክብር ለሚኖሩ ሁሉ ሕይወት አጭር የመከራ ጊዜ መከተሉ አይቀርም።
ዔሳውና ይሁዳ አስቆሮታዊ የኃጢአትን ደስታ እየተከተሉ እንደ ሥጋ ኖረዋል፣ በመጨረሻም የመንግሥተ ሰማይን በረከቶች አጥተዋል። ይሁን እንጂ ሙሴ፣ ያዕቆብ፣ ዳንኤልና ሦስቱ ጓደኞቹ የሰማይን ደስታ ከፍ አድርገው በመመልከት መከራዎችን አሸንፈዋል። በተመሳሳይ፣ የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን አባላት እግዚአብሔር ቃል በገባላቸው የሰማይ ደስታ ላይ ተስፋቸውን በማድረግ፣ እርሱ ባዘዘው መሠረት የአዲሱ ኪዳን የሰንበት ቀንና የፋሲካን በረከቶች ለመስበክ ራሳቸውን ይሰጣሉ።
ሙሴ ካደገ በኋላ፣ የፈርዖን የልጅ ልጅ መባልን በእምነት እንቢ አለ። ለጥቂት ጊዜ በኀጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ፣ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋራ መከራን መቀበል መረጠ። ከግብጽ ሀብት ይልቅ ስለ ክርስቶስ መከራን መቀበል እጅግ የሚበልጥ ሀብት መሆኑን ተገነዘበ፤ ወደ ፊት የሚቀበለውን ብድራት ከሩቅ ተመልክቷልና። ዕብራውያን 11:24–26
119 የቡንዳንግ ፖ.ሳ.ቁ፣ ቡንዳንግ-ጉ፣ ሲኦንግናም-ሲ፣ ግዮንጊ-ዶ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ስልክ 031-738-5999 ፋክስ 031-738-5998
ዋና ምስሪያ ቤት፡ 50፣ ሱኒ_ሮ ፣ ቡንዳኔግ_ጉ፣ ሲዮንግያም_ሲ፣ ግዋንጊዶ_ሲ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ዋና ቤተ ክርስቲያን፡ 35፣ ፓንግዮዬክ_ ሮ ቡንዳንግ _ጉ፣ ሶንግያም ሲ፣ ጊዮኔጊ_ዱ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
World Mission Society Church of God ሁሉም መብቶች የተጠብቁ ናቸው። ግላዊ ደኅንነት