ኖኅ መርከቡን ሲሠራ ለረጅም ጊዜ ብቸኝነት ቢያጋጥመውም በአምላክ በረከት ያምን ነበር። ሙሴ በግብፅ ልዑል ሆኖ ክብሩን ከመደሰት ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መርጧል። ሐዋርያው ጳውሎስ ብዙ ችግሮች ቢያጋጥሙትም መንግሥተ ሰማያትን ለሰዎች የማቅረብ እድል በማግኘቱ ተደስቷል። በተመሳሳይ፣ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን አባላት መስቀላቸውን ተሸክመው በደስታ በእምነት መንገድ ይሄዳሉ።
የሰማይ እናት ሁሌም ታስታውሰናለች፣ “የመንግሥተ ሰማያት ተስፋ የለንምን?” ስለዚህ በግንባር ቀደምትነት የሚሠሩት ቅዱሳን ወይም መጋቢዎች፣ ሁሉም የራሳችንን መስቀሎች ስንሸከም በዓይኖቻችን ፊት ከሚፈጠሩት መሰናክሎች ባሻገር የተዘጋጀውን የመንግሥተ ሰማያትን በረከቶች መመልከት ይኖርብናል።
ከግብፅ ሀብት ይልቅ ስለ ክርስቶስ መከራን መቀበል እጅግ የሚበልጥ ሀብት መሆኑን ተገነዘበ፤ ወደ ፊት የሚቀበለውን ብድራት ከሩቅ ተመልክቷልና። ዕብራውያን 11፥26
እንደ ሥጋ ብትኖሩ ትሞታላችሁና፤ ክፉ የሆነውን የሥጋ ሥራ በመንፈስ ብትገድሉ ግን፣ በሕይወት ትኖራላችሁ፤ በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና። ልጆች ከሆን ወራሾች ደግሞ ነን፤ የክብሩ ተካፋዮች እንሆን ዘንድ በርግጥ የመከራው ተካፋዮች ብንሆን፣ . . . የአሁኑ ዘመን ሥቃያችን ወደ ፊት ሊገለጥ ካለው፣ ለእኛ ከተጠበቀልን ክብር ጋር ሲነጻጸር ምንም እንዳይደለ እቈጥራለሁ። ሮሜ 8፥13-18
119 የቡንዳንግ ፖ.ሳ.ቁ፣ ቡንዳንግ-ጉ፣ ሲኦንግናም-ሲ፣ ግዮንጊ-ዶ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ስልክ 031-738-5999 ፋክስ 031-738-5998
ዋና ምስሪያ ቤት፡ 50፣ ሱኒ_ሮ ፣ ቡንዳኔግ_ጉ፣ ሲዮንግያም_ሲ፣ ግዋንጊዶ_ሲ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ዋና ቤተ ክርስቲያን፡ 35፣ ፓንግዮዬክ_ ሮ ቡንዳንግ _ጉ፣ ሶንግያም ሲ፣ ጊዮኔጊ_ዱ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
World Mission Society Church of God ሁሉም መብቶች የተጠብቁ ናቸው። ግላዊ ደኅንነት