ልክ የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ራሱ የተነገረውን ትንቢት እንዳገኘና እስራኤላውያንን ከምርኮ ነፃ እንዳወጣና በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ እንደገነባ ሁሉ እኛም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተመዘገቡትን ትንቢቶች ማመን አለብን። እንደ ቂሮስ ሁሉ እኛም በዚያው ጥልቅ ደስታ ተሞልተን እግዚአብሔር ያዘዘንን ወንጌል በፍጹም ልባችንና በፍጹም ነፍሳችን መስበክ አለብን።
ኢየሱስ በአሥሩ ምናን ምሳሌ እንዳስተማረው፣ የእግዚአብሔርን ቃል ለሚፈሩ ሰዎች የከበረ የወደፊት ጊዜ እንደሚመጣ ቃል ገብቷል፤ በመንግሥተ ሰማያትም ለዘላለም ከእግዚአብሔር ጋር ይነግሣሉ፤ ዘላለማዊ ክብርንም ያጣጥማሉ፤ ሞት፣ ሐዘን፣ ልቅሶ ወይም ሥቃይ በማይኖርበት ስፍራ።
ከዚህ በኋላ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር አየሁ፤ የመጀመሪያው ሰማይና የመጀመሪያዪቱ ምድር ዐልፈዋልና፤ ባሕርም ከእንግዲህ ወዲህ አይኖርም። . . .እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት ወይም ሐዘን ወይም ልቅሶ ወይም ሥቃይ አይኖርም፤ የቀድሞው ሥርዐት ዐልፏልና።” ራእይ 21:1–4
119 የቡንዳንግ ፖ.ሳ.ቁ፣ ቡንዳንግ-ጉ፣ ሲኦንግናም-ሲ፣ ግዮንጊ-ዶ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ስልክ 031-738-5999 ፋክስ 031-738-5998
ዋና ምስሪያ ቤት፡ 50፣ ሱኒ_ሮ ፣ ቡንዳኔግ_ጉ፣ ሲዮንግያም_ሲ፣ ግዋንጊዶ_ሲ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ዋና ቤተ ክርስቲያን፡ 35፣ ፓንግዮዬክ_ ሮ ቡንዳንግ _ጉ፣ ሶንግያም ሲ፣ ጊዮኔጊ_ዱ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
World Mission Society Church of God ሁሉም መብቶች የተጠብቁ ናቸው። ግላዊ ደኅንነት