እስራኤላውያን በወጡበት ወቅት፣ በመላው ግብፅ ላይ አደጋዎች ደረሱ፣ ነገር ግን በእስራኤላውያን ላይ ምንም ዓይነት አደጋዎች አልደረሱም። ይህ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ባለበት ቦታ እና የሌለበት ቦታ መካከል ያለው ልዩነት ምረጋገጫ ነበር። እግዚአብሔር የአዲሱ ኪዳን ፋሲካ የትም ቢከበር፣ ሕዝቡ ሲገቡ ይባረካሉ፣ ሲወጡም ይባረካሉ፣ በምድርም ላይ ካሉ አሕዛብ ሁሉ በላይ ከፍ እንደሚያደርጋቸው ታላቅ ተስፋ ሰጥቷል።
ነብያት ኢሳይያስ፣ ሶፎንያስና ጴጥሮስ በዚህች ምድር ላይ ታላቅ የእሳት ጥፋት እንደሚመጣ ይመሰክራሉ፤ ምክንያቱም ዓለም የእግዚአብሔርን የሰንበት ቀንና የፋሲካን በዓል ጨምሮ አዲሱን ኪዳን አላከበረም። መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ልጅ የአብ ክርስቶስ አህንሳንግሆንግ እና የእግዚአብሔር እናት ልጆች መሆንና ከሁሉም አደጋዎች የእግዚአብሔርን ጥበቃ ማግኘት የሚችለው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን በመጠበቅ ብቻ እንደሆነ ይመሰክራል።
ለአምላክህ ለ እግዚአብሔር በፍጹም ብትታዘዝና እኔ ዛሬ የምሰጥህን ትእዛዙን ሁሉ በጥንቃቄ ብትከተል፣ አምላክህ እግዚአብሔር በምድር ላይ ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ በላይ ከፍ ያደርግሃል። አምላክህን እግዚአብሔር ን ብትታዘዝ፣ እነዚህ በረከቶች ሁሉ ያንተ ይሆናሉ፤ አይለዩህምም። . . . ስትገባ ትባረካለህ፤ ስትወጣም ትባረካለህ። ዘዳግም 28:1–6
“ይህን ሁሉ ለዚህ ሕዝብ በምትነግርበት ጊዜ ሰዎቹ፣ ‘እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ታላቅ ጥፋት በእኛ ላይ ለምን ዐወጀ? በደላችንስ ምንድን ነው? በአምላካችንስ በ እግዚአብሔር ላይ የሠራነው ኀጢአት ምንድን ነው?’ ብለው ቢጠይቁህ፣ እንዲህ ትላቸዋለህ፤ ‘አባቶቻችሁ እኔን ስለ ተዉኝ ነው’. . . ኤርምያስ 16:10–11
119 የቡንዳንግ ፖ.ሳ.ቁ፣ ቡንዳንግ-ጉ፣ ሲኦንግናም-ሲ፣ ግዮንጊ-ዶ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ስልክ 031-738-5999 ፋክስ 031-738-5998
ዋና ምስሪያ ቤት፡ 50፣ ሱኒ_ሮ ፣ ቡንዳኔግ_ጉ፣ ሲዮንግያም_ሲ፣ ግዋንጊዶ_ሲ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ዋና ቤተ ክርስቲያን፡ 35፣ ፓንግዮዬክ_ ሮ ቡንዳንግ _ጉ፣ ሶንግያም ሲ፣ ጊዮኔጊ_ዱ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
World Mission Society Church of God ሁሉም መብቶች የተጠብቁ ናቸው። ግላዊ ደኅንነት