የእግዚአብሔር ልጆች እንደ እግዚአብሔር ትምህርት የዓለም ጨውና ብርሃን ሲሆኑ፣ በመልካም ሥራቸው የእግዚአብሔርን ክብር ሲያሳዩና የሰውን ልጅ በአዲሱ ኪዳን እውነት ወደ እግዚአብሔር ሲመሩ፣ በፊቱ በሚቆሙበት ቀን እግዚአብሔር ይደሰታል፤ የተትረፈረፈ በረከትም ይሰጣቸዋል።
በመንፈስ ቅዱስ ዘመን ክርስቶስ አህንሳንግሆንግንና ኢየሩሳሌም የሰማይ እናትን ከተቀበልን፣ ከአሁን ጀምሮ ከዓለም የተማርናቸውን ክፉ ልማዶች ትተን እንደ ክርስቲያን አዲሱን ሰው መልበስ አለብን። ይህ ዓለም ከጊዜ ወደ ጊዜ እግዚአብሔርን መምሰል እያጣ፣ ጠማማና ክፉ እየሆነ ሲመጣ፣ ልክ እንደ ኖኅና ሎጥ ዘመን የእግዚአብሔር የፍርድ ቀን እንደቀረበ ተገንዝበን ይበልጥ እግዚአብሔርን በመምሰል መኖር አለብን።
እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ሰውነታችሁን ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕያው መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም እንደ ባለ አእምሮ የምታቀርቡት አምልኳችሁ ነው። መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሯችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12:1–2
119 የቡንዳንግ ፖ.ሳ.ቁ፣ ቡንዳንግ-ጉ፣ ሲኦንግናም-ሲ፣ ግዮንጊ-ዶ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ስልክ 031-738-5999 ፋክስ 031-738-5998
ዋና ምስሪያ ቤት፡ 50፣ ሱኒ_ሮ ፣ ቡንዳኔግ_ጉ፣ ሲዮንግያም_ሲ፣ ግዋንጊዶ_ሲ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
ዋና ቤተ ክርስቲያን፡ 35፣ ፓንግዮዬክ_ ሮ ቡንዳንግ _ጉ፣ ሶንግያም ሲ፣ ጊዮኔጊ_ዱ፣ የኮሪያ ሪፐብ.
World Mission Society Church of God ሁሉም መብቶች የተጠብቁ ናቸው። ግላዊ ደኅንነት